ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክት፣ ሥራን የሚያከብር፣ በሥራ የሚያምን፣ ሥራን የመፍጠር ብቃት ያለው፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳት አሻሽሎ በመስራት በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በኩል ለተጠቃሚ ሕብረተሰብ በማድረስ ሙሉ የሆነ የእንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለእንተርፕራይዞች በመስጠት የትራንስፎርሜሽን ዕቅድን በማሳካት ከክልሉ ሥራ አጥንትን እና ድህነትን መቀነስ።
የቴ/ሙ/ት/ና ሥልጠና ዘርፍ በግንባር ቀደምነት በተለዋጭና ውጤት ተኮር ስትራቴጂዎችና ዕቅዶቹ መሰረት ባደረገ የሥልጠና ሥርዓት በገበያ ጥናት ላይ የተመሠረተ ሥልጠና በመስጠት ሥራ ፈጥኖ ራስን ለማስተዳደር የሚችሉ በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል በጥራትና በብቃት ማፍራትና የአከባቢውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት በማጥናት ገንዘብን፣ ጊዜና ጉልበትን ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን ቀድቶና አሻሽሎ በመሥራት በእንተርፕራይዞች በኩል ለተጠቃሚው ማድረስና የተሟላ የእንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለእንተርፕራይዞች በመስጠት የክልሉ የልማት ዕቅዶች ተግባራዊ እንድሆኑ ኮሌጁ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ።